Academics & Admission

ትምህርቶችና የመግቢያ መመዘኛዎች

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ በሶስት ደረጃ የተከፋፈሉ የትምህርት ፕሮግራሞች ይኖሩታል፡፡ የመጀመሪያው የሠርተፊኬት ፕሮግራም፣ ሁለተኛው የዲፕሎማ ፕሮግራም፣ ሶሰተኛው የዲግሪ ፕሮግራም ናቸው፡፡

አስተውሎ

ይኸ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ የተዘጋጀው በሙሉ ጊዜአቸው እየሰሩ በትርፍ ጊዜአቸው ለሚማሩ ተማሪዎች ነው፡፡

 • ትምህርቶቹ ሁሉ ሶስት ክሬዲት ያላቸው ሆነው በብሎክ ኮርስ መሰረት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ማለትም አንድ ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ ተመዝግበውና ተምረው ሲጨርሱ ብቻ የሚቀጥለውን ትምህርት መውሰድ ይችላሉ፡፡
 • አንድ ትምህርት በአራት ሳምንት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ አምስተኛው ሳምንት የማጥኛ፣ የፈተና መውሰጃና ያለተጠናቀቁ ስራዎችን አጠናቆ የማስረከቢያ ሳምንት ይሆናል፡፡
 • የትምህርቱ ሳምንት ሰኞ ተጀምሮ እሁድ የሚያልቅ ነው፡፡
 • አንድ የዳነ ክርስትያን ከዚህ በታች የታዘዙትንና መለኪያዎችን ሁሉ ፈጽሞ ከሰርተፊኬት ጀምሮ፣ ዲፕሎማውን አጠናቆ ዲግሪውን ጨርሶ በዲግሪ ለመመረቅ የሚፈጅበት ጊዜ አምስት አመት ነው፡፡ta
 1. የሠርተፊኬት ፕሮግራም

በቤተክርስትያንዋ ኮሌጅ የሚካሄደው የሠርተፊኬት ፕሮግራም የአንድ አመት ፕሮግራም ነው፡፡ ፕሮግራሙ የሚሰጠው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡ 

Read More

ባጠቃላይ እያንዳንዳቸው ሶስት የሰሚስተር ሰአቶች ዋጋ ያላቸው ስምንት ትምህርቶች በሰርተፊኬት ፕሮግራሙ ይሰጣሉ፡፡ አንድ ጌታ እየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለና ክርስትያን የሆነ ተማሪ፣ የሠርተፊኬት ፕሮግራሙን ለመጨረስና ሠርተፊኬቱን ለማግኘት ስምንቱንም ኮርሶች ተምሮ፣ ትምህርቶቹን ለመጨረስ ማረጋገጫ የሚሆኑ መመዘኛዎችን ያለምንም ጉድለት አሟልቶ፣ 24 የኮርስ ሰአቶችን ማሟላት አለባቸው፡፡

የኮሌጁ ሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የሠርተፊኬት ፕሮግራም ትምህርቶችን በመማር የሚጀምሩ ናቸው፡፡

1.1. በእየዓመቱ የሚሰጡ የሠርተፊኬት ኮርሶች

1. የዮሐንስ ወንጌል ጥናት (The Gospel of John)

2. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኪዳናት (Bible Covenants)

3. ስልጣንና መገዛት (Submission)

4. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዶግማ (Bible Doctrine)

5. መንፈስ ቅዱስና ስጦታዎቹ (Holy Spirit and His Gifts)

6. በመንፈሳዊነት ማደግ (Spiritual Growth)

7. ገላትያና የሮሜ መልእክቶች (Galatians and Romans)

8. የመጨረሻው ዘመን (End Times)

1.2. የተማሪ ውጤቶች

 

Read More

የተማሪዎች የትምህርት ውጤቶቹ በሁለት መንገድ ይዳሰሳሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ትምህርት ተማሪዎች የሚሰሯቸው በጽሑፍ የሚቀርቡ አራት የግልና የቡድን ስራዎች ከሰላሳ በመቶ ሲወሰዱ ቀሪው ሰባ በመቶ የትምህርቱ የመጨረሻው ፈተና ውጤት ይሆናል፡፡ የውጤት አሰጣጡ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

 • ከ 90% እና ከ90% በላይ A
 • ከ 80% እና ከ80% እስከ 89% B
 • ከ 60% እና ከ60% እስከ 79% C
 • ከ 40% እና ከ40% እስከ 59% D
 • ከ 39% በታች F

1.3. ለሠርተፊኬት ፕሮግራሙ የመግቢያ መመዘኛዎች

ለዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ሰርተፊኬት ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው፡፡

Read More

 • በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ አምነው የዳኑ ክርስትያኖች
 • በእየቤተክርስትያኖቻቸው የሚሰጠውን የድነት ትምህርት ተምረው ያጠናቀቁ
 • በኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት መሰረት ቢያንስ 8ኛ ክፍል ያጠናቀቁ
 • በሚገባ አማርኛ ማንበብ፣ መጻፍና ያነበቡትን ማገናዘብ የሚችሉ
 • ባጠቃላይ በግልም ሆነ በቡድን የሚሰጡ ስራዎችን ለማከናወን ቢያንስ በሳምንት ስድስት ሰአቶች መመደብ የሚችሉ
 • በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ትምህርቱን ለማጠናቀቅ የሚችሉና የተሰጣቸውን ስራዎችና ፈተናቸውን በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚችሉ
 1. የዲፕሎማ ፕሮግራም

በቤተክርስትያንዋ ኮሌጅ የሚካሄደው የዲፕሎማ ፕሮግራም ከሠርተፊኬት ፕሮግራሙ ቀጥሎ የሚካሄድ በእራሱ የሁለት አመት ፕሮግራም ነው፡፡ ፕሮግራሙ የሚሰጠው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡

Read More

በዚሁ ኮሌጅ በሠርተፊኬት ፕሮግራሙ የተወሰዱት ትምህርቶች ውጤታቸው B ና ከዛ በላይ የሆኑ ትምህርቶች በዲፕሎማ ፕሮግራም ውስጥ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡

ከሠርተፊኬቱ በተጨማሪ በዲፕሎማ ፕሮግራሙ ባጠቃላይ እያንዳንዳቸው ሶስት የሰሚስተር ሰአቶች ዋጋ ያላቸው አስራ ስድስት ትምህርቶች በዲፕሎማ ፕሮግራሙ ይሰጣሉ፡፡ አንድ ጌታ እየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለና ክርስትያን የሆነ ተማሪ፣ የዲፕሎማ ፕሮግራሙን ለመጨረስና ዲፕሎማውን ለማግኘት አስራስድስቱንም ኮርሶች ተምሮ፣ ትምህርቶቹን ለመጨረስ ማረጋገጫ የሚሆኑ መመዘኛዎችን ያለምንም ጉድለት አሟልቶ፣ 48 የኮርስ ሰአቶችን ማሟላት አለባቸው፡፡

አስተውሉ የኮሌጁ ሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የሠርተፊኬት ፕሮግራም ትምህርቶችን በመማር የሚጀምሩ ናቸው፡፡

2.1. በእየዓመቱ የሚሰጡ የመጀመሪያው ዓመት ዲፕሎማ ኮርሶች

Read More

1. የእምነት መርሆዎች (Principles of Faith)

5. የሐዋሪያት ሥራ (Acts)

2. የመሪነት መርሆዎች (Principles of Leadership)

6. የፀሎት መርሆዎች (Principles of Prayer)

3. መለኮታዊ ፈውስ (Divine Healing)

7. ጽድቅ (Righteousness)

4. አዲስ ጅማሮ (New beginings)

8. ወንጌል ስርጭት (Evangelism and Outreach)

2.2. በእየዓመቱ የሚሰጡ የሁለተኛው ዓመት የዲፕሎማ ኮርሶች

Read More

1. አዲስ ጅማሮ (New beginings)

5. የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ 2 (Old Testament Survey 2)

2. በመንፈሳዊነት ማደግ (Spiritual Growth)

6. በአእምሮ መታደስ (Renewing the Mind)

3. የእየሱስ ክርስቶስ ሕይወት (Life of Christ)

7. የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ 1 (New Testament Survey 1)

4. የብሉይ ኪዳን ዳሰሳ 1 (Old Testament Survey 1)

8. የአዲስ ኪዳን ዳሰሳ 2 (New Testament Survey 2)

 

2.3. የተማሪ ውጤቶች

Read More

የተማሪዎች የትምህርት ውጤቶቹ በሁለት መንገድ ይዳሰሳሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ትምህርት ተማሪዎች የሚሰሯቸው በጽሑፍ የሚቀርቡ አራት የግልና የቡድን ስራዎች ከሰላሳ በመቶ ሲወሰዱ ቀሪው ሰባ በመቶ የትምህርቱ የመጨረሻው ፈተና ውጤት ይሆናል፡፡ የውጤት አሰጣጡ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

 • ከ 90% እና ከ90% በላይ A
 • ከ 80% እና ከ80% እስከ 89% B
 • ከ 60% እና ከ60% እስከ 79% C
 • ከ 50% እና ከ50% እስከ 59% D
 • ከ 49% እና ከ49% በታች F
2.4. ለዲፕሎማ ፕሮግራሙ የመግቢያ መመዘኛዎች

ለዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ የዲፕሎማ ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው፡፡

Read More

 • በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ አምነው የዳኑ ክርስትያኖች
 • በእየቤተክርስትያኖቻቸው የሚሰጠውን የድነት ትምህርት ተምረው ያጠናቀቁ
 • በዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ የሚሰጠውን የሰርተፊኬት ፕሮግራም አጠናቀው ያለፉ (የሰርተፊኬት ፕሮግራሙ ውጤት B ና ከ B በላይ የሆነ ውጤታቸው ለዲፕሎማው ፕሮግራም ይወሰድላቸዋል)
 • በኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት መሰረት ቢያንስ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ
 • በሚገባ አማርኛ ማንበብ፣ መጻፍና ያነበቡትን ማገናዘብ የሚችሉ
 • ባጠቃላይ በግልም ሆነ በቡድን የሚሰጡ ስራዎችን ለማከናወን ቢያንስ በሳምንት ስድስት ሰአቶች መመደብ የሚችሉ
 • በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ትምህርቱን ለማጠናቀቅ የሚችሉና የተሰጣቸውን ስራዎችና ፈተናቸውን በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ ለማስረከብ የሚችሉ
 1. የዲግሪ ፕሮግራም

በመጽሐፍ ኮሌጁ የሚካሄደው የዲፕሎማ ፕሮግራም ከዲፕሎማው ፕሮግራሙ ቀጥሎ የሚካሄድ በእራሱ የሁለት አመት ፕሮግራም ነው፡፡ ፕሮግራሙ የሚሰጠው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡

Read More

በዚሁ ኮሌጅ በሠርተፊኬትና በዲፕሎማው ፕሮግራም የተወሰዱት ትምህርቶች ውጤታቸው B ና ከዛ በላይ የሆኑ ትምህርቶች በዲግሪው ፕሮግራም ውስጥ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፡፡

ከሠርተፊኬቱና ከዲፕሎማው ትምህርቶች በተጨማሪ በዲግሪው ፕሮግራም ባጠቃላይ እያንዳንዳቸው ሶስት የሰሚስተር ሰአቶች ዋጋ ያላቸው አስራ ስድስት ትምህርቶች በዲግሪ ፕሮግራሙ ይሰጣሉ፡፡ አንድ ጌታ እየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኙ አድርጎ የተቀበለና ክርስትያን የሆነ ተማሪ፣ የዲግሪ ፕሮግራሙን ለመጨረስና ዲግሪውን ለማግኘት አስራ ስድስቱንም ኮርሶች ተምሮ፣ ትምህርቶቹን ለመጨረስ ማረጋገጫ የሚሆኑ መመዘኛዎችን ያለምንም ጉድለት አሟልቶ፣ 48 የኮርስ ሰአቶችን መጨረስ አለበት፡፡

አስተውሉ የኮሌጁ ሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የሠርተፊኬት ፕሮግራም ትምህርቶችን በመማር የሚጀምሩና በዲፕሎማው አልፈው ወደ ዲግሪ የሚደርሱ ናቸው፡፡

3.1. በእየዓመቱ የሚሰጡ የመጀመሪያው ዓመት የዲግሪ ኮርሶች

Read More

Lorem ipsum dolor sit amet, consectetur adipiscing elit. Ut elit tellus, lu

1. ፔንታቱክ 1 (Pentateuque 1)

5. የቤተክርስትያን ታሪክ  2 (Church History 2)

2. ፔንታቱክ 2 (Pentateuque 2)

6. የእግዚአብሔር መንግስት 1 (Kingdom of God 1)

3.  ወንጌላት (The Gospels)

7. የእግዚአብሔር መንግስት 2 (Kingdom of God 2)

4.  የቤተክርስትያን ታሪክ 1 (Church History 1)

8. ተልእኮ (Mission)

ctus nec ullamcorper mattis, pulvinar dapibus leo.

3.2. በእየዓመቱ የሚሰጡ የሁለተኛው ዓመት የዲግሪ ኮርሶች

Read More

1. የማማከር አገልግሎት (Counseling) 1

5. የአነስተኛ ህብረቶች አገልግሎት (Cell Ministry)

2. የማማከር አገልግሎት (Counseling) 2

6. የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ (Hermenetics)

3. ዕብራዊያን (Hebrew)

7. የጥናታዊ ጽሁፍ አጻጻፍ (writing a research paper)

4. እግዚአብሔርን ማምለክ (Praise and Worship)

8. የመመረቂያ ጽሁፍ (Graduation thesis)

3.3. የተማሪ ውጤቶች

የተማሪዎች የትምህርት ውጤቶቹ በሁለት መንገድ ይዳሰሳሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ትምህርት ተማሪዎች የሚሰሯቸው በጽሑፍ የሚቀርቡ ስራዎች ሲኖሩ እነዚህ አርባ በመቶ ይይዛሉ፡፡ ቀሪው ስልሳ በመቶ የትምህርቱ የመጨረሻው ፈተና ውጤት ይሆናል፡፡ የውጤት አሰጣጡ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

Read More

 • ከ 90% እና ከ90% በላይ A
 • ከ 80% እና ከ80% እስከ 89% B
 • ከ 60% እና ከ60% እስከ 79% C
 • ከ 50% እና ከ50% እስከ 59% D
 • ከ 49% እና ከ49% በታች F

3.4. ለዲግሪ ፕሮግራሙ የመግቢያ መመዘኛዎች

ለዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ የዲግሪ ፕሮግራም ተመዝጋቢዎች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው፡፡

Read More

 • በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ አምነው የዳኑ ክርስትያኖች
 • በእየቤተክርስትያኖቻቸው የሚሰጠውን የድነት ትምህርት ተምረው ያጠናቀቁ
 • በዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ የሰርተፊኬትና የዲፕሎማ ፕሮግራም አጠናቀው ያለፉ (የሰርተፊኬት ፕሮግራሙ ውጤት B ና ከ B በላይ የሆነ ውጤታቸው ለዲፕሎማው ፕሮግራም ይወሰድላቸዋል)
 • በኢትዮጵያ የትምህርት ስርአት መሰረት ቢያንስ 12 ክፍል ያጠናቀቁ
 • በሚገባ አማርኛ ማንበብ፣ መጻፍና ያነበቡትን ማገናዘብ የሚችሉ
 • ባጠቃላይ በግልም ሆነ በቡድን የሚሰጡ ስራዎችን ለማከናወን ቢያንስ በሳምንት አስር ሰአቶችን መመደብ የሚችሉ
 • በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ትምህርቱን ለማጠናቀቅ የሚችሉና የተሰጣቸውን ስራዎችና ፈተናቸውን በተሰጣቸው ጊዜ ውስጥ ለማስረከብ የሚችሉ

በዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ (IEECBC) በመማር ሂደት ውስጥ ሲገቡ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነገሮች ይገንዘቡ፡

 1. ለመማር ሲመዘገቡና መማር ሲጀምሩ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና (ማቲ 5፡ 6) የሚለውን ጥቅስ ያስተውሉ፣ ያሰላስሉ፣ በምድር ላይ ሲኖሩ ምኞትዎም ይሁን፡፡
 2. ሁልጊዜ ወደመማር ሲመጡ ቢያንስ ለትምህርቱ ተብሎ የተሰጥዎትንና ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁሉ በአጠገብዎ ያድርጉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስዎትንም አይርሱ፡፡
 3. እያንዳንዱ ትምህርት በእየአንድ ሳምንት ተከፋፍሎ በአራት ሳምንት ውስጥ የሚያልቅ ሲሆን አምስተኛው ሳምንት የፈተና ጊዜ ይሆናል፡፡
 4. የእያንዳንዱ የሳምንት ትምህርት የመጀመሪያ ጊዜ ሰኞ ነው፡፡
 5. በእያንዳንዱ ሳምንት ውስጥ፡

Read More

ለትምህርቱ ተብሎ እንዲያነቡ የታዘዙትን ሁሉ በሚገባ ያንብቡ፣

 • ለትምህርቱ ተብሎ እንዲያዳምጡ የታዘዙትን ትምህርቶች በሳምንት ውስጥ ደጋግመው ያድምጡ፣
 • በሳምንቱ ውስጥ ለተሰጥዎት ትምህርት የተሰጥዎትን ጥያቄዎች በሚገባ አንብበው፣ ጥያቄዎቹ በሚያዙት መሰረት መልስዎን ይጻፉ፣
 • በሳምንቱ ለተሰጥዎት ጥያቄዎች የጻፉትን መልስ ሁልጊዜ በሳምንቱ መጨረሻ ቀን (እሁድ) መልስዎን ታይፕ አድርገው ወይም በጥሩ የአማርኛ የእጅ ጽሁፍ ጽፈውና ፎቶግራፍ አንስተው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ይጫኑት
 • ፈተናው በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ እለት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በስንት ሰአትና እንዴት ፈተናዎን እንደሚሰሩና በስንት ሰአት ውስጥ እንደሚያጠናቅቁ በዝርዝር ይገለጣል፡፡
 1. በአምስት ሳምንት ውስጥ ኮርሱን ካላጠናቀቁ ተጨማሪ ሁለት ሳምንት ይሰጥዎታል፡፡ ለዚህ አስፈላጊውን ሙሉ ወጪ እንዲሸፍኑ ግን ይገደዳሉ፡፡ በዚህ ሙሉ ወጪዎትን ሸፍነው በሁለት ሳምንት ውስጥ እንዲጨርሱ በተደረጉበት ጊዜ ውስጥ ትምህርቶን ካልጨረሱ ትምህርቶን እንዳልወሰዱ ተቆጥሮ እንደአዲስ ተማሪ ከመጀመሪያው ጀምረው ኮርሱ በሚቀጥለው በሚሰጥበት ወቅት ጠብቀው እንዲወስዱ ይገደዳሉ፡፡ ይኸ ደግሞ ለተጨማሪ ወጪና ለተጨማሪ ጊዜ ይዳርጎታል፡፡
 2. ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ትምህርቱን ለሚያስተምረው አስተማሪ በቀጥታ በኢሜል ወይም በስልኩ አድራሻ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ቦታ ላይም ጥያቄዎችን መጫን ይቻላል፡፡
 3. የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጁ የሠርተፊኬት፣ የዲፕሎማና የዲግሪ ፕሮግራሞቹ የሚሰጡት በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡ ከትምህርቶቹ ጋር የተያያዙት የቤት ስራዎችና ፈተናዎች ሁሉ በአማርኛ የሚቀርቡ ሲሆን ተማሪዎችም መልሶቻቸውንና ስራዎቻቸውን ሁሉ በአማርኛ ያቀርባሉ፡፡
 4. ኮሌጁ ለአንዳንድ ማስተባበሪያ ወጪዎች መሸፈኛ US $60 በእየ ኮርሱ እንዲያዋጡ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም ስጦታዎችንና ሌሎች መዋጮዎችን ኮሌጁ ይቀበላል፡፡

Our Teachers
Disclaimer (ማሳሰቢያ)

የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጁ የሚያስተምራቸው በመጽሐፍ ቅዱስና በክርስትና እምነት ላይ የተመሰረቱ ትምህርቶችን ነው፡፡ ትምህርቶቹ በቤተክርስትያናችን የእምነት አንቀጽ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ ኮሌጁ ከInternational Victory Bible Institute (IVBI) ጋር ትብብር ሲኖረው ከTransworld  Accrediting Commission International እውቅናም አለው ነው፡፡

 1. እነዚህንም ትምህርቶች ተምረው ላጠናቀቁ ተማሪዎች እንደ ደረጃቸው ሰርተፊኬት፣ ዲፕሎማና ዲግሪዎችን ይሰጣል፡፡ በኮሌጁ የሚሰጡት ትምህርቶች የመደበኛ የቀለምና የሙያ ትምህርቶች ስላልሆኑ የሚሰጡትም ሰርተፊኬቶች፣ ዲፕሎማዎችና ዲግሪዎች ለዚህ ጉዳይ የሚውሉ አይደሉም፡፡
 2. የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጁ ለሚያስተምረው ትምህርት (tution) አያስከፍልም፡፡ እንደ ሁኔታዎች ለማስተባበሪያ፣ ለህትመትና ለመሳሰሉት ወጪዎች መሸፈኛ የሚውል ክፍያ ተማሪዎች እንዲጋሩ ግን ይደረጋል፡፡