About Us

የዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ (IEECBC) ተልእኮ

ሰዎች በመንፈሳዊ ህይወታቸው ተለውጠው፣ በዚህ አለም በቅድስና መኖር እንዲችሉ ለመርዳት የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መጽሐፍ ኮሌጅ (IEECBC) የማስተማር ስራውን የጀመረው በ January 2015 ነው፡፡ የማስተማር ስራውን የሚያካሂደው በዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን ስር በመደራጀት፣  ከ International Victory Bible Institute (IVBI) ጋር በመተባበር (in affiliation)ና ከTransworld Accrediting Commission International እውቅናን (accreditation) በማግኘት ነው፡፡

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን የሚከተሉት ተልእኮ፣ ራዕይና እሴቶች ያላት ናት፡፡
ተልእኮ

ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ሁሉ በመስበክ፣በመመስከርና በማስተማር የኢየሱስ ደቀመዝሙር ማድረግ፡፡

ራዕይ

በወንጌል የሚድኑትን ማብዛት፣ የዳኑትን ለሁለንተናዊ ፍሬያማነት ማብቃትና ለበረከት እንዲሆኑ ማሰማራት፡፡

ቶች
  • እየሱስን ማዕከል ያደርገ አስተምህሮት
  • የአጥብያ ቤተክርስቲያንን አሰራር ማዕከል ያደረገ
  • በአገልጋይነት ላይ የተመሰረተ አገልግሎት

ከላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጁ የተመሰረተበት ቤተክርሰትያን የማንነት መገለጫዎችን መሰረት በማድረግ የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ የሚከተሉት ሶሰት ግቦች አሉት፡፡

የዓለምአቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ የሚከተሉት ሦስት ግቦች ይኖሩታል፡፡
  • ክርስቶስን ያማከሉና በህይወትና በተግባር የሚተረጎሙ የመጽሐፍ ቅደስ ትምህርቶችን ማቅረብ፡፡ ጌታ እየሱስ ክርስቶስ በሰራው የደህንነት ስራ አምነው የዳኑ አማኞች በእግዚአብሔር ቃል እውቀት ላይ የተመሰረተ መንፈሳዊ እድገት እንዲኖራቸው ለማገዝና ጌታ እየሱስ ክርሰቶስን መስለው መንፈሳዊ ፍሬ እንዲያፈሩ ማብቃት
  • ቀዳማይ ሆነው ጌታ እየሱስ ክርስቶስን እየመሰሉ የሚያገለግሉ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ማፍራት፡፡
  • የትምህርት ሽፋኑን ዓለም አቀፍ በማድረግ የማስተማር አድማሱን አማርኛ ተናጋሪዎች ባሉበት ሁሉ ማስፋት

 

 

 

 

 

“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

ማቴ 28:19