Home

Quick Links (ፈጣን ገጾች)


Registration (ምዝገባ)


Join Class (ወደ ክፍል)


Give here (ልገሳ)

Current Message (ሰሞነኛ መልእክት)

ወድቀናልና ለመነሳት ንስሃ እንግባ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱትን ወረርሽኞች ሁሉ ስናጠና ለወረርሽኞች መነሳት ዋናና መሰረታዊ ምክንያት ሰው እግዚአብሔርን አንፈልግህም አንታዘዝህምም ማለት እንደሆነ እንማራለን፡፡ COVED-19 ወረርሽኝም እንዲሁ እግዚአብሔርን ያለመታዘዝ ውጤት ነው፡፡
አሁን ያለነው ዓለምን በሙሉ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አስገብቶ፣ መንግስታት አለን የሚሉትን ሃብት፣ ገንዘብና እውቀት ሁሉ እያስገበረ ያለ ግን አሁንም ጦርነቱን ገና ያልተሸነፈ የዓለም አቀፍ ወረርሽኝ (COVED-19) ውስጥ ነው፡፡ ካስተዋልነው በዚህ ውስጥ የእግዚአበሔር መኖርና ማንነት የተገለጠበት የእኛ ማንነትም የተገለጠበት ነው፡፡
Read More

በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እግዚአብሔር ለዓለም እኔ እግዚአብሔር አለሁ፣ ብቸኛ ሉአላዊና ሁሉን ቻይ እንደሆንኩ እወቁ፣ ከመጥፎ ስራችሁም ተመለሱ፣ መዳንም ይሁንላችሁ እያለ ነው፡፡ ዓለም ያስጥለኛል ብላ የምታስባቸውና ያላት ነገሮች ሁሉ (ገንዘብ፣ እወቀት፣ቴክኖሎጂ ወዘተ) ከአንድ ቫይረስ እንኳን የማያስጥላት መሆኑን እያየንም ነው፡፡

ድነናል፣ የእግዚአብሔር ልጆች ነን፣ እግዚአብሔር ይናገረናል ለምንል ለእኛ ለክርስትያኖችስ በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ያለው መልእክት ምንድን ነው? እግዚአብሔር ስታችኋል፣ አልታዘዛችሁኝም ስለዚህ በአፋችሁ ከእኔ ጋር በልባችሁ ግን ከእኔ ጋር አይደላችሁም እያለ ነው፡፡ እኔ አምላክ እንደሆንኩ እወቁ፣ ወደ እኔ ተመለሱ፣ የንስሃ ፍሬንም አፍሩ እያለም ነው፡፡ ያለን አንድ ምርጫ ብቻ ነው፣ እርሱም ወደ እግዚአብሔር መመለስና እግዚአብሔርን መታዘዝ ብቻ ነው፡፡

በጌታ የሆናችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ሁሉ እስቲ ይኸን አስተውሉ፡፡ እኛ በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ የሆንነው በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ካልሆኑት ጋር በዚህ በምድር ላይ አብረን እንኖራለን፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ካልሆኑትና በዓለም ጋር ካሉት ጋር የምንለየው እግዚአብሔር የሚለውን ሰምተን የምንታዘዝ ስንሆን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ሳንታዘዝ የእግዚአብሔር መሆን አንችልም፡፡  ስለእግዚአብሔር ብዙ የምንናገር ግን እግዚአብሔርን የማንታዘዝ መሆናችን አሁን በአደባባይ የተገለጠ እውነት ነው፡፡

እግዚአብሔርን እንዳልታዘዘው እንደአንዱ ክርስትያን እራሴን እንደምሳሌ ላቅርብ፡፡ በክርስትና ውስጥ ባለኝ እድሜና እግዚአብሔር በቤተክርስትያነ ውስጥ በሰጠኝ ሃላፊነት መሰረት እኔ ዛሬ የሆነውን ትናንትና አውቄ ዛሬን አምልጬ ማስመለጥ ነበረብኝ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጁ በዚህ ጊዜ እንደሚዘጋ አስቀድሜ አውቄ፣ ለዚህ ጊዜ የሚሆን አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጌ፣ መማር ማስተማሩ ላንድ ቀን እንኳን ሳይስተጓጎል እንዲካሄድ ማድረግ ነበረብኝ፡፡ እኔ ግን የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጃችን እንደሚዘጋ ያወኩት ነገሮችን በመገጣጠም ካገኘሁት መረዳት ተነስቼ ነው፡፡ ታዲያ ከእግዚአብሐር ጋር ነኝ እያልኩ፣ እግዚአብሔርን መስማት ይቻላል ብዮ እያስተማርኩ፣ እግዚአብሔርን ታዘዙ እያልኩም እያስተማርኩም ይኸን ሁኔታ አስቀድሞ አለማወቄ ምን ይባላል? ማወቅ ግን ነበረብኝ፡፡ ምናልባት አንዳንዶቻችሁ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ ነገሮችን ይሰውራል ትሉኝ ይሆናል፡፡ አትልፉ እግዚአብሔር እንዲህ አይነቱን አይሰውርም፡፡  

አሁን ወዲያና ወዲህ ሳልል ስለእራሴ ፍርጥ አድርጌ ለእግዚአብሔር እንዲህ ብዮ ነገርኩት፡ እግዚአብሔር ሆይ አልሰማሁህም፣ በአስቀመጥከኝ ቦታም ታማኝ አልሆንኩም፣ በጌታ በእየሱሱ ክርስቶስ ይቅር በለኝ አልኩት፡፡  ቸርነቱ፣ ምህረቱና ጸጋው የበዛ አምላክም ይቅር ብሎኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ዋናው ስራዬ ማስተማር አይደለም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መሆኔን ማረጋገጥ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን እየመሰለን ከእግዚአብሔር ጋር የሌለን ብዙ ነን፡፡ አንዳንዶቻችን (ለምሳሌ እኔ) ስለእግዚአብሔር ብዙ ስለተናገርን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ይመስለናል፡፡ ነገን ከእግዚአብሔር ሰምቶ የማያውቅ መንፈሳዊ እውር ነው፡፡

ውድ ክርስትያኖች ወገኖቼ ነገን ከእግዚአብሔር ጋር ሆናችሁ፣ እግዚአብሔርን ሰምታችሁ፣ እግዚአብሔርን ታዛችሁ በአሸናፊነት የዚህቺን ዓለም ህይወት ትጨርሱ ዘንድ ዛሬን በንስሃ ተመለሱ፡፡ የእግዚአብሔር ምህረት፣ ቸርነትና ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡ አሜን!


How to Join Class using a Laptop
( ላፕቶፕን በመጠቀም ክፍሉን እንዴት እንደሚቀላቀል)How to Join Class using a Phone
( ስልክ በመጠቀም ክፍልን እንዴት እንደሚቀላቀል)

https://videos.files.wordpress.com/qW2TziF7/how-to-join-webex-meeting-from-phone_new-3_hd.mp4

Our Community (ማህበራዊ ሕይወት )

ጌታ እየሱስ ክርስቶስን እየመሰሉ በመንፈሳዊ ህይወታቸው የሚያድጉ የእየሱስ ክርስቶስ ደቀመዝሙሮችና አገልጋዮች እንዲፈሩ ቤተክርስትያንን ማገዝ  የዓለምአቀፍ የኢተዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ (IEECBC) የተፈጠረበት ምክንያት ነው፡፡ ይኸን ተግባራዊ ማድረጊያ አንዱ መንገድ ተማሪዎች በእየአካባቢያቸው አነስተኛ ቡድኖችን እንዲያቋቁሙና በነዚህ ቡድኖች ውስጥ ሆነው እንዲፀልዩ፣ የእግዚአብሔርን ቃል እንዲከፋፈሉ፣ የቤት ስራቸውን እንዲወያዩበትና፣ ፈተናቸውን አብረው እንዲያጠኑ ማበረታታት ነው፡፡

 

 
Our Mission (ተልእኮ)

ሰዎች በመንፈሳዊ ህይወታቸው ተለውጠው፣ በዚህ አለም በቅድስና መኖር እንዲችሉ ለመርዳት የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መጽሐፍ ኮሌጅ (IEECBC) የማስተማር ስራውን የጀመረው በ January 2015 ነው፡፡ የማስተማር ስራውን የሚያካሂደው በዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን ስር በመደራጀት፣  ከ International Victory Bible Institute (IVBI) ጋር በመተባበር (in affiliation)ና ከTransworld Accrediting Commission International እውቅናን (accreditation) በማግኘት ነው፡፡

Class Meeting Numbers

Thursday (6pm – 9pm)

  • Certificate: 126 572 1177
  • Diploma: 126 261 3414
  • Degree: 126 677 2801

Saturday (9am – 1pm)

  • Certificate:126 733 5979
  • Diploma:126 216 4428
  • Degree:126 329 1166